What We Believe

As we are affiliated with Assemblies of God (AG) in United States of America, we adopt their beliefs. Their beliefs are based on the Bible and emphasize the work of the Holy Spirit, evangelism, and a personal relationship with Jesus Christ. Here are some key doctrines:

  1. The Bible as God’s Word

      The AG believes the Bible is the inspired and infallible Word of God, serving as the ultimate authority for faith and practice.

      2. Salvation through Jesus Christ

      Salvation is received by grace through faith in Jesus Christ (Ephesians 2:8-9). This includes repentance, forgiveness of sins, and being spiritually born again.

      3. Baptism in the Holy Spirit

      A central belief is that after salvation, believers should seek the baptism in the Holy Spirit, which is distinct from and follows conversion. The initial physical evidence of this baptism is speaking in tongues (Acts 2:4).

      4. Gifts and Power of the Holy Spirit

      The AG teaches that the Holy Spirit empowers believers with gifts such as healing, prophecy, and speaking in tongues (1 Corinthians 12). These gifts are for the edification of the Church and are active today.

      5. Divine Healing

      They believe in divine healing as part of Christ’s atonement (Isaiah 53:5) and that prayer can bring physical healing.

      6. The Second Coming of Christ

      The AG believes in the imminent return of Jesus Christ (the rapture) and the millennial reign (Christ ruling on earth for 1,000 years).

      7. Water Baptism and Communion

      Water Baptism – Performed by immersion as a public declaration of faith.•

      Holy Communion – A symbolic remembrance of Christ’s sacrifice.

      8. The Church and Evangelism

      The AG emphasizes global evangelism, believing the Church’s mission is to spread the Gospel and disciple believers worldwide.

      የእምነት አንቀጽ

      አዲስ ኪዳን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በቦስተን የጠቅላላ ጉባዔ እግዚአብሔር ሕብረት የደቡብ ኒው ኢንግላንድ ቅርንጫፍ ጉባኤ እግዚአብሔር አባል ስትሆን ለወንጌል ሥራ እንደ አስፈላጊነቱ ከሌሎችም ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሕብረት ታደርጋለች።

      እኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ከዚህ ቀጥለው በተገለጹት መሠረታዊ ሐሳቦች ያለምንም ለውጥ በፍፁምና ባንድ ልብ አምነን እንቀበላለን።

      • መጽሐፍ ቅዱስ፤ (በብሉይና በአዲስ ኪዳን የሚገኙት ስልሳ ስድስት መጻህፍት) ቅዱሳን ስዎች በእግዚአብሔር መንፈስ በመነዳት እንደጻፉትና ምንም ስህተት የሌለበት ስልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን።
      • እግዚአብሔር በሦስት አካላት ዘላለማዊ በሆነ መንገድ በሚኖር አንድ አምላክ እናምናለን፤ እነዚህም አካላት አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ እናምናለን።
      • ኢየሱስ ክርስቶስ የሥላሴ አካል እንደሆነ፤ ከድንግል ማርያም በመወለድ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም እንዳገለገለ፤ የሰውን ልጅ ለመቤዠት ደሙን እንዳፈሰሰ፣ እንደሞተ፣ እንደተቀበረና በሦስተኛውም ቀን በአካላዊ ትንሳኤ በመነሳት በአብ ቀኝ እንደተቀመጠ፤ እንዲሁም ቅዱሳንን ሊሸልምና በዓለምም ላይ ሊፈርድ በክብርና በኃይል እንደሚመጣ እናምናለን።
      • መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አካልና አምላክ እንደሆነ፤ ዓለምን ስለ ኃጢአት፤ ስለ ፍርድና ስለ ጽድቅ በመውቀስ ክርስቶስን እንደሚያከብር፤ በቅዱሳን በማደር ቅዱሳንን ለቅድስና ሕይወትና ለአገልግሎት እንደሚያዘጋጅ፤ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽና ዕድገት መንፈሳዊ ስጦታዎችን፤ እንደወደደ እንደሚሰጥ እናምናለን።
      • ድነት በክርስቶስ የመስቀል ሞትና ትንሳኤ ያለ አንዳች የሰው ጥረት በእግዚአብሔር ጸጋ እንደሚገኝ፤ ይህም ድነት በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አሰራር በእምነት ብቻ እውን እንደሚሆን እናምናለን።
      • በክርስቶስ ኢየሱስ ጌትነትና አዳኝነት በሚያምኑ አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን መካከል በሚሆን የመንፈስ አንድነትና ኅብረት እናምናለን።